በአለም አቀፍም ደረጃ ተላላፊ በሽታዎች በረካቶችን ለህመም እና ሞት በመዳረግ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ተላላፊ በሽታዎች በተለይ በታዳጊ ሃገራት ለሚከሰት ሀመም እና ሞት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው፡፡የተወሰኑት ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ፡፡ለምሳሌ ያህል በቅርቡ የተከሰተው እና አለምን ያሰጨነቀው ኮሮና (ኮቪድ) ተጠቃሽ ነው፡፡ኮሌራም አልፎ አልፎ በታዳጊ አገሮች እንዲሁም ድርቅ እና የሰላም እጦት በተከሰተባቸው ቦታዎች በወረርሽኝ መልክ ይከሰታል፡፡ቲቢ እና ኤች አይ ቪ ኤድስም ከተላላፊ በሽታዎች መካከል ለአለም ማህበረሰብ ተግዳሮት ሆነው እንደቀጠሉ ነው፡፡ወባ፣አሜባ፣ታይፎይድ እና ታይፈስም በዚህ መጽሐፍ ተዳስሰዋል፡፡እነ ኩፍኝ፣ ቋቁቻ እና የጉበት ቫይረስም ተተንትነዋል፡፡በድምሩ ከ60 በላይ ተላላፊ በሽታዎች በዚህ መጽሐፍ ይገኛሉ፡፡ የተላላፊ በሽታዎቹ መተላለፊያ መንገዶች እና የመከላከያ ዘዴዎች የተለየ ትኩረት ተችሯቸዋል፡፡የህክምና አማራጮችም እንዲሁ ጠቅለል ተደርገው ተቀምጠዋል፡፡አስፈላጊ ቦታዎች ላይ የበሽታዎቹ አመጣጥ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ይህ መጽሐፍ ለጤና እና ህክምና ተማሪዎች እንደ አጋዥ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ለአጠቃላዩ ማህበረሰብ ደግሞ ስለ በሽታዎች መንስኤ እና መከላከያ መንገዶች በቂ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡